3 ፈረሰኛው ይጋልባል፤ሰይፍ ይንቦገቦጋል፤ጦር ያብረቀርቃል፤የሞተው ብዙ ነው፤ሬሳ በሬሳ ሆኖአል፤ስፍር ቍጥር የለውም፤መተላለፊያ አልተገኘም።
4 ይህ ሁሉ የሆነው ቅጥ ባጣች፣አሳሳችና መተተኛ በሆነች ዘማዊት ምክንያት ነው፤እርሷም በዝሙቷ አሕዛብን፣በጥንቈላዋም ሕዝቦችን ባሪያ ያደረገች ናት።
5 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ፤ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልበዋለሁ፤ዕርቃንሽን ለአሕዛብ፣ኀፍረትሽንም ለነገሥታት አሳያለሁ።
6 ቍሻሻ እደፋብሻለሁ፤እንቅሻለሁ፤ማላገጫም አደርግሻለሁ።
7 የሚያዩሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሹ፣‘ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል?’ ይላሉ፤የሚያጽናናሽንስ ከወዴት አገኛለሁ?”
8 አንቺ በዐባይ ወንዝ አጠገብ ካለችው፣በውሃ ከተከበበችው፣ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን?ወንዙ መከላከያዋ፣ውሃውም ቅጥሯ ነው።
9 ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።