3 አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥየምትኖር፣መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ለራስህም፣“ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?” የምትል፣የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።
4 እንደ ንስር መጥቀህ ወደ ላይ ብትወጣ፣ጐጆህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፣ከዚያ አወርድሃለሁ”ይላል እግዚአብሔር።
5 “ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ዘራፊዎችም በሌሊት ቢገቡ፣የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለምን?ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ጥቂት ቃርሚያ አይተዉምን?አንተ ግን ምንኛ ጥፋት ይጠብቅሃል!
6 ዔሳው ግን እንዴት ተዘረፈ?የሸሸገውስ ሀብት ምንኛ ተመዘበረ!
7 ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ድንበር ይገፉሃል፤ጓደኞችህ ያታልሉሃል፤ ያሸንፉህማል፤እንጀራህን የበሉ ወጥመድ ይዘረጉብሃል፤አንተ ግን አታውቀውም።
8 “በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?”ይላል እግዚአብሔር።
9 ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ተገድሎ ይጠፋል።