4 መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤እንደ ጦር ፈረስም ይጋልባሉ።
5 ገለባ እንደሚበላ እንደሚንጣጣ እሳት፣ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኀያል ሰራዊት፣የሠረገሎችን ድምፅ የሚመስል ድምፅ እያሰሙ፣በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ።
6 በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤የሁሉም ፊት ይገረጣል።
7 እንደ ተዋጊዎች ድንገት አደጋ ይጥላሉ፤እንደ ወታደሮችም ቅጥርን ይዘላሉ፤ከመንገዳቸውም ሳይወጡ፣አቅጣጫ ይዘው ይጓዛሉ።
8 እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤እያንዳንዱ መስመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤መስመራቸውን ሳይለቁ፣መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ።
9 ከተማዪቱን ይወራሉ፤በቅጥሩም ላይ ይዘላሉ፤በቤቶች ላይ ዘለው ይወጣሉ፤እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ።
10 ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤ሰማይም ይናወጣል፤ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ከዋክብትም ከእንግዲህ ወዲያ አያበሩም።