14 ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፣ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቦአል፤ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ፣ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና።
15 ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ከዋክብትም ከእንግዲህ አያበሩም።
16 እግዚአብሔር ከጽዮን ጮኾ ይናገራል፤ከኢየሩሳሌም ያንጐደጒዳል፤ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፣ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
17 “ከዚያም እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር፣በቅዱሱ ተራራዬ በጽዮን እንደምኖር ታውቃላችሁ፤ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፤ከእንግዲህም ወዲያ ባዕዳን አይወሯትም።
18 “በዚያ ጊዜ ተራሮች፣ አዲስ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤ኰረብቶችም ወተት ያፈሳሉ፤በይሁዳ ያሉ ሸለቆዎች ሁሉ ውሃ ያጐርፋሉ፤ ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይፈልቃል፤የሰጢምን ሸለቆ ያጠጣል።
19 ግብፅ ባድማ፣ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ፣በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና።
20 ይሁዳ ለዘላለም፣ኢየሩሳሌምም ለትውልድ ሁሉ መኖሪያ ትሆናለች፤