1 ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው ንግር፤
2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣አንተ የማትሰማው እስከ መቼ ነው?“ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው?
3 ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ?እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ?ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ፤ጠብና ግጭት በዝቶአል።
4 ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፤ፍትሕ ድል አይነሣም፤ፍትሕ ይጣመም ዘንድ፣ክፉዎች ጻድቃንን ይከባሉ።
5 “ቢነገራችሁም እንኳ፣የማታምኑትን እናንተን፣በዘመናችሁ አንድ ነገር ስለማደርግ፣እነሆ፤ ሕዝቡን እዩ፤ ተመልከቱም፤እጅግም ተደነቁ።