2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ዝናህን ሰምቻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህም አስፈራኝ፤በእኛ ዘመን አድሳቸው፤በእኛም ጊዜ እንዲታወቁ አድርግ፤በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።
3 እግዚአብሔር ከቴማን፣ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። ሴላክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ውዳሴውም ምድርን ሞላ።
4 ጸዳሉ እንደ ፀሓይ ብርሃን ነው፤ጨረር ከእጁ ወጣ፤ኀይሉም በዚያ ተሰውሮአል።
5 መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው።
6 ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤መንገዱ ዘላለማዊ ነው።
7 የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን?መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን?በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ፣በጋለብህ ጊዜ፣በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን?