5 መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው።
6 ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤መንገዱ ዘላለማዊ ነው።
7 የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን?መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን?በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ፣በጋለብህ ጊዜ፣በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን?
9 ቀስትህን አዘጋጀህ፤ፍላጻም እንዲመጣልህ አዘዝህ፤ ሴላምድርን በወንዞች ከፈልህ፤
10 ተራሮች አዩህ፤ ተጨነቁም፤የውሃ ሞገድ ዐልፎ ሄደ፤ቀላዩ ደነፋ፤ማዕበሉንም ወደ ላይ አነሣ።
11 ከሚወረወሩ ፍላጾችህ፣ከሚያብረቀርቅ የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣም፣ፀሓይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ።