7 የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን?መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን?በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ፣በጋለብህ ጊዜ፣በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን?
9 ቀስትህን አዘጋጀህ፤ፍላጻም እንዲመጣልህ አዘዝህ፤ ሴላምድርን በወንዞች ከፈልህ፤
10 ተራሮች አዩህ፤ ተጨነቁም፤የውሃ ሞገድ ዐልፎ ሄደ፤ቀላዩ ደነፋ፤ማዕበሉንም ወደ ላይ አነሣ።
11 ከሚወረወሩ ፍላጾችህ፣ከሚያብረቀርቅ የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣም፣ፀሓይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ።
12 በምድር ላይ በመዓት ተመላለስህ፤ሕዝቦችንም በቊጣ ረገጥሃቸው።
13 ሕዝብህን ለመታደግ፣የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤የክፋትን ምድር መሪ ቀጠቀጥህ፤ከራስ ጠጒሩ እስከ እግር ጥፍሩም ዕርቃኑን አስቀረኸው። ሴላ