1 ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ መንፈሱ ታወከ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ።
2 ያለመውንም ሕልም እንዲነግሩት ንጉሡ ጠንቋዮችን፣ አስማተኞችን፣ መተተኞችንና ኮከብ ቈጣሪዎችን እንዲጠሩ አዘዘ፤ እነርሱም ገብተው በፊቱ ቆሙ፤
3 እርሱም፣ “አንድ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም ምን እንደሆነ ለማወቅ መንፈሴ ተጨንቆአል” አላቸው።
4 ከዚያም ኮከብ ቈጣሪዎቹ ለንጉሡ በአረማይክ ቋንቋ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ! ሕልምህን ለአገልጋዮችህ ንገረን፤ እኛም እንፈታልሃለን” አሉት።