32 የነቢያት መናፍስት ለነቢያት ይታዘዛሉ፤
33 እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም።በቅዱሳን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲሁ ነው፤
34 ሴቶች በጉባኤ ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤
35 ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።
36 የእግዚአብሔር ቃል የወጣው ከእናንተ ነውን? ወይስ የደረሰው ወደ እናንተ ብቻ ነውን?
37 ማንም ነቢይ ነኝ የሚል ወይም መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ የሚል ቢኖር፣ ይህ የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ መሆኑን ይወቅ፤
38 ይህን የማያውቅ ቢሆን ግን እርሱም አይታወቅ።