20 እናንተ ግን ከእርሱ ከቅዱሱ፣ ቅባት አላችሁና፤ ሁላችሁም እውነትን ታውቃላችሁ።
21 እኔ የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፤ ነገር ግን እውነትን ስለምታውቁትና ከእውነት ምንም ውሸት ስለማይወጣ ነው።
22 ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ሐሰተኛ ማነው? ይህ አብንና ወልድን የሚክደው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
23 ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድን የሚያምን ሁሉ አብም አለው።
24 ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ውስጥ ይኑር፤ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ውስጥ ቢኖር፣ እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።
25 ይህ እርሱ የሰጠን ተስፋ የዘላለም ሕይወት ነው።
26 ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ።