10 ስለዚህ፣“ሕይወትን የሚወድ፣መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ምላሱን ከክፉ፣ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።
11 ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም፤
12 ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።”
13 መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?
14 ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራ ቢደርስባችሁ ብፁዓን ናችሁ፤ “ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።”
15 ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
16 በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ አክፋፍተው የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።