15 ኢየሱስ ሐሳባቸውን አውቆ ከዚያ ዘወር አለ። ብዙ ሕዝብም ተከተለው፤ ሕመምተኞችን ሁሉ ፈወሰ፤
16 ማንነቱን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
17 ይህም የሆነው በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፤
18 “እነሆ የመረጥሁት፣የምወደውና በእርሱ ደስ የሚለኝ አገልጋዬ፣መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤እርሱም ለአሕዛብ ፍትሕን ያውጃል።
19 አይጨቃጨቅም ወይም አይጮኽም፤ድምፁም በአደባባይ አይሰማም።
20 ፍትሕን ለድል እስኪያበቃ ድረስ፣የተቀጠቀጠውን ሸምበቆ አይሰብርም፤የሚጤሰውንም የጧፍ ክር አያጠፋም።
21 አሕዛብ በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።”