34 ኢየሱስም፣ “ለመሆኑ ስንት እንጀራ አላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።እነርሱም፣ “ሰባት እንጀራና ጥቂት ትናንሽ ዓሣ” አሉት።
35 እርሱም ሕዝቡን መሬት ላይ እንዲቀመጡ አዘዛቸው፤
36 ሰባቱን እንጀራና ዓሣውን ይዞ ካመሰገነ በኋላ ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለሕዝቡ አከፋፈሉ።
37 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ደቀ መዛሙርቱም የተረፈውን ቊርስራሽ ሰባት መሶብ ሙሉ አነሡ።
38 የበሉትም ከሴቶችና ከሕፃናት ሌላ አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ።
39 ኢየሱስ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ በጀልባ ወደ መጌዶል ሄደ።