11 ከዚያም ዲያብሎስ ትቶት ሄደ፤ መላእክትም መጥተው አገለገሉት።
12 ኢየሱስ የዮሐንስን መታሰር በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ተመለሰ።
13 የናዝሬትንም ከተማ ትቶ፣ በዛብሎንና በንፍታሌም አካባቢ በባሕሩ አጠገብ በምትገኘው በቅፍርናሆም ከተማ መኖር ጀመረ።
14 በዚህም በነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፤
15 “የዛብሎን ምድር፣ የንፍታሌም ምድር፣ከዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ አጠገብ፣ያለው የአሕዛብ ገሊላ፣
16 በጨለማ የሚኖር ሕዝብ፣ታላቅ ብርሃን አየ፤በሞት ጥላ ምድር ላለው፣ብርሃን ወጣለት።”
17 ከዚያ ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ፣ “ንስሓ ግቡ፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና” እያለ መስበክ ጀመረ።