ቈላስይስ 4:6-12 NASV

6 ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ በጨው እንደ ተቀመመ ሁል ጊዜ በጸጋ የተሞላ ይሁን።

7 ቲኪቆስ ስላለሁበት ሁኔታ በሙሉ ይነግራችኋል፤ እርሱ የተወደደ ወንድምና ታማኝ አገልጋይ፣ በጌታም አብሮኝ ሎሌ ነው።

8 ስላለንበት ሁኔታ እንድታውቁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ለዚህ ጒዳይ ወደ እናንተ እልከዋለሁ፤

9 እርሱም ከእናንተ ወገን ከሆነው ከታማኙና ከተወዳጁ ወንድማችን ከአናሲሞስ ጋር ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱም እዚህ ስላለው ሁኔታ ሁሉ ይነግሯችኋል።

10 አብሮኝ የታሰረው አርስጥሮኮስና የበርናባስ የአክስቱ ልጅ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ስለ ማርቆስ መመሪያ ደርሶ አችኋል፤ እንግዲህ ወደ እናንተ ሲመጣ ተቀበሉት።

11 ኢዮስጦስ የተባለው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙት መካከል ለእግዚአብሔር መንግሥት አብረውኝ የሚሠሩት እኔንም ያጽናኑኝ እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም አጽናንተውናል።

12 ከእናንተ ወገን የሆነው የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተረጋግታችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋደለ ነው።