16 ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ።
17 ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ።
18 በመንፈስ ተሞሉ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ብክነት ነውና።
19 በመዝሙርና በውዳሴ፣ በመንፈሳዊም ዝማሬ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ በልባችሁ ለጌታ ተቀኙ፤ አዚሙም።
20 በዚህም እግዚአብሔር አብን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር ሁል ጊዜ አመስግኑ።
21 ለክርስቶስ ካላችሁ አክብሮታዊ ፍርሀት የተነሣ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ተገዙ።
22 ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁም ተገዙ