10 ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተበመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።
11 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
12 እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”
13 እግዚአብሔር፣“ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?
14 መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?