2 በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን።
3 እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራ ቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
4 ስለዚህ የወረሰው ስም ከመላእክት ስም እንደሚበልጥ ሁሉ፣ እርሱም ከመላእክት እጅግ የላቀ ሆኖአል።
5 እግዚአብሔር፣“አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤”ወይስ ደግሞ፣“እኔ አባት እሆነዋለሁ፤እርሱም ልጅ ይሆነኛል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?
6 ደግሞም እግዚአብሔር በኵሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣“የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል።
7 ስለ መላእክትም ሲናገር፣“መላእክቱን ነፋሳት፣አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል።
8 ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤“አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል፤