4 ስለዚህ የወረሰው ስም ከመላእክት ስም እንደሚበልጥ ሁሉ፣ እርሱም ከመላእክት እጅግ የላቀ ሆኖአል።
5 እግዚአብሔር፣“አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤”ወይስ ደግሞ፣“እኔ አባት እሆነዋለሁ፤እርሱም ልጅ ይሆነኛል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?
6 ደግሞም እግዚአብሔር በኵሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣“የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል።
7 ስለ መላእክትም ሲናገር፣“መላእክቱን ነፋሳት፣አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል።
8 ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤“አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል፤
9 ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣የደስታንም ዘይት ቀባህ።”
10 ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተበመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።