32 ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ፣ በመከራ ውስጥ በብርቱ ተጋድሎ ጸንታችሁ የቆማችሁበትን የቀድሞውን ዘመን ዐስቡ።
33 አንዳንድ ጊዜ በአደባባይ ለስድብና ለስደት ተጋልጣችሁ ነበር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደዚህ ያለ መከራ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋር አብራችሁ መከራን ተቀብላችኋል።
34 እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ።
35 ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።
36 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ የተስፋ ቃሉን እንድትቀበሉ፣ ጸንታችሁ መቆም ያስፈልጋችኋል፤
37 ምክንያቱም ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣“የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም።
38 ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ፣ነፍሴ በእርሱ ደስ አትሰኝም።”