35 ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።
36 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ የተስፋ ቃሉን እንድትቀበሉ፣ ጸንታችሁ መቆም ያስፈልጋችኋል፤
37 ምክንያቱም ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣“የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም።
38 ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ፣ነፍሴ በእርሱ ደስ አትሰኝም።”
39 እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን እንጂ፣ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት አይደለንም።