5 ሙሴ ወደ ፊት ስለሚነገረው ነገር እየመሰከረ፣ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ እንደ አንድ ታማኝ አገልጋይ ነበር፤
6 ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ልጅ ነው። እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።
7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣
8 በምድረ በዳ በፈተና ቀን፣በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ልባችሁን አታደንድኑ።
9 አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤መረመሩኝ፤ ያደረግሁትንም ሁሉ ለአርባ ዓመት አዩ።
10 በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤እንዲህም አልሁ፤ ‘ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል፤መንገዴንም አላወቁም፤’
11 ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤“ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም።”