1 በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
2 እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ።
3 ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም።
4 ሕይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች።
5 ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም።