5 “እንግዲህ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ይሁን እንጂ ከእናንተ፣ ‘የምትሄደው የት ነው?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
6 ይህን በመናገሬም ልባችሁ በሐዘን ተሞልቶአል፤
7 ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መሄዴ ይበጃችኋል። እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድሁ ግን እርሱን ወደ እናንተ እልካለሁ፤
8 በሚመጣበትም ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሳል።
9 ስለ ኀጢአት ሲባል፣ ሰዎች በእኔ ስለማያምኑ ነው፤
10 ስለ ጽድቅ፣ ወደ አብ ስለምሄድና ከእንግዲህ ስለማታዩኝ ነው፤
11 ስለ ፍርድም፣ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።