1 ከዐሥራ አራት ዓመት በኋላም፣ ዳግመኛ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤ በዚህ ጊዜ ከበርናባስ ጋር ነበርሁ፤ ቲቶንም ይዤው ሄጄ ነበር።
2 ካገኘሁትም መገለጥ የተነሣ ወደዚያ ሄድሁ፤ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል ለእነርሱም ገለጥሁላቸው። ይሁን እንጂ፣ ምናልባት በከንቱ እየሮጥሁ ወይም ሮጬ እንዳይሆን በመሥጋት፣ ዋነኞች ለሚመስሉት ብቻ በግል ይህን አስታወቅኋቸው።
3 ከእኔ ጋር የነበረው ቲቶ እንኳ የግሪክ ሰው ቢሆንም፣ እንዲገረዝ አልተገደደም ነበር።
4 ይህ ጒዳይ የተነሣው አንዳንድ ሐሰተኞች ወንድሞች በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነውን ነጻነት ሊሰልሉና ባሪያዎች ሊያደርጉን ወደ እኛ ሾልከው በመግባታቸው ነው።
5 ለእነዚህ ሰዎች ለአንድ አፍታ እንኳ አልተገዛንላቸውም፤ ይኸውም፣ የወንጌል እውነት ከእናንተ ጋር ጸንቶ እንዲኖር ነው።
6 ዋነኛ መስለው ስለሚታዩት ሰዎች ማንነት እኔን አይገደኝም፤ እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፤ እነዚህም ሰዎች ለመልእክቴ የጨመሩልኝ ነገር የለም።