1 “እስራኤል ገና ሕፃን ሳለ ወደድሁት፤ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት።
2 እስራኤል ግን አብዝቼ በጠራኋቸው ቍጥር፣አብዝተው ከእኔ ራቁ፤ለበኣል አማልክት ሠዉ፤ለምስሎችም ዐጠኑ።
3 ኤፍሬምን እጁን ይዤ፣እንዲራመድ ያስተማርሁት እኔ ነበርሁ፤ነገር ግን የፈወስኋቸው እኔ እንደሆንሁ፣እነርሱ አላስተዋሉም።
4 በሰው የርኅራኄ ገመድ፣በፍቅርም ሰንሰለት ሳብኋቸው፤ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ አነሣሁላቸው፤ዝቅ ብዬም መገብኋቸው።
5 “ታዲያ ንስሓ መግባትን እምቢ በማለታቸው፣ወደ ግብፅ አይመለሱምን?አሦርስ አይገዛቸውምን?