5 በንጉሣችን የበዓል ቀን፣አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤እርሱም ከፌዘኞች ጋር ተባበረ።
6 ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤በተንኰል ይቀርቡታል፤ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤እንደሚነድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል።
7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዦቻቸውን ፈጁ፤ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።
8 “ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው።
9 እንግዶች ጒልበቱን በዘበዙ፤እርሱ ግን አላስተዋለም።ጠጒሩም ሽበት አወጣ፤እርሱ ግን ልብ አላለም።
10 የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤እርሱንም አልፈለገም።
11 ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤አንድ ጊዜ ወደ ግብፅ ይጣራል፤ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።