1 አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ከበባ ተደርጎብናልና፤የእስራኤልን ገዥ፣ጒንጩን በበትር ይመቱታል።
2 “አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣አመጣጡ ከጥንት፣ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣የእስራኤል ገዥ፣ከአንቺ ይወጣልኛል።”
3 ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣እስራኤል ትተዋለች፤የተቀሩት ወንድሞቹም፣ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።
4 በእግዚአብሔር ኀይልበአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል።በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ተደላድለው ይኖራሉ።
5 እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።አሦራዊ ምድራችንን ሲወር፣ምሽጐቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ሰባት እረኞችን፣እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።