5 ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ፣ተቸግረው በየመንገዱ ላይ ተንከራተቱ፤ሐምራዊ ግምጃ ለብሰው ያደጉ፣አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተኙ።
6 በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት፣የማንም እጅ ሳይረዳት፣በድንገት ከተገለበጠችው፣ሰዶም ላይ ከደረሰው ቅጣት ይልቅ ታላቅ ነው።
7 መሳፍንቶቻቸው ከበረዶ ይልቅ ብሩህ፣ከወተትም ይልቅ ነጭ ነበሩ፤ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቍ የቀላ፣መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበር።
8 አሁን ግን ከጥላሸት ይልቅ ጠቍረዋል፤በመንገድም የሚያውቃቸው የለም፤ቆዳቸው ከዐጥንታቸው ጋር ተጣብቆአል፤እንደ ዕንጨትም ደርቀዋል።
9 በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣በራብ ደርቀው ያልቃሉ።
10 ሕዝቤ ባለቀበት ጊዜ፣ምግብ እንዲሆኑአቸው፣ርኅሩኆቹ ሴቶች በገዛ እጆቻቸው፣ልጆቻቸውን ቀቀሉ።
11 እግዚአብሔር ለመቅሠፍቱ መውጫ በር ከፈተ፤ጽኑ ቍጣውን አፈሰሰ፤መሠረትዋን እንዲበላ፣በጽዮን እሳት ለኰሰ።