40 ቀጥሎም ምስጋና ያቀረቡት ሁለቱ የመዘምራን ቡድኖች፣ በእግዚአብሔር ቤት ቦታቸውን ያዙ፤ እኔም ከግማሾቹ ሹማምት ጋር ቦታዬን ያዝሁ፤
41 እንደዚሁም ካህናቱ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሐናንያ መለከታቸውን ይዘው፣
42 መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላምና ኤጽር ቦታቸውን ያዙ፤ መዘምራኑ በይዝረሕያ መሪነት ዘመሩ።
43 እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።
44 በዚያን ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበት ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የእርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሰኝተው ነበርና።
45 እንደ መዘምራኑና በር ጠባቂዎቹ ሁሉ፣ እነዚህም የአምላካቸውን አገልግሎትና የመንጻቱን ሥርዐት በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ፈጸሙ።
46 ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ።