3 የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤አዳር፣ ጌራ፣ አቢሁድ፣
4 አቢሱ፣ ናዕማን፣ አሖዋ፣
5 ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።
6 በጌባ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤
7 ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
8 ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።
9 ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣