16 “ ‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤የፈረሰውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ።ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤እንደ ገናም እሠራዋለሁ፤
17 ይኸውም የቀሩት ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉ፣ስሜን የተሸከሙ አሕዛብም እንዲሹኝ ነው፤እነዚህን ያደረገ ጌታ እንዲህ ይላል፤’
18 እነርሱም ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው።
19 “ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን አሕዛብ እንዳናስጨንቃቸው ይህ የእኔ ብያኔ ነው።
20 ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኵሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤
21 የሙሴ ሕግማ ከጥንት ጀምሮ በየሰንበቱ በምኵራብ ሲነበብና በየከተማው ሲሰበክ ኖሮአልና።”
22 በዚህ ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከመላው ቤተ ክርስቲያን ጋር ሆነው ከመካከላቸው አንዳንድ ሰዎችን መርጠው፣ ከጳውሎስና ከበርንባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ከወንድሞችም መካከል ዋነኛ የነበሩትን በርስያን የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ፤