13 እነርሱም እንደ ገና፣ “ስቀለው!” እያሉ ጮኹ።
14 ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን የፈጸመው ወንጀል አለ” አላቸው።እነርሱ ግን፣ “ስቀለው!” እያሉ የባሰ ጮኹ።
15 ጲላጦስም ሕዝቡን ደስ ለማሰኘት ሲል በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።
16 ወታደሮቹ ፕራይቶሪዮን ወደተባለ ወደ ገዡ ግቢ ወሰዱት፤ ሰራዊቱንም ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ።
17 ቀይ ልብስም አለበሱት፤ የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በራሱ ላይ ደፉበት።
18 ከዚያም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ እጅ ነሡት፤
19 ራሱንም በበትር መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።