4 ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ኢየሱስ ወዳለበት መቅረብ ስላልቻሉ፣ የቤቱን ጣራ እርሱ ባለበት በኩል ነድለው ቀዳዳ በማበጀት ሽባው የተኛበትን ዐልጋ በዚያ አወረዱ።
5 ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፣ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል!” አለው።
6 በዚያ ተቀምጠው የነበሩ አንዳንድ ጸሐፍት ስለዚህ ነገር በልባቸው እያሰላሰሉ፣
7 “ይህ ሰው እንዴት እንዲህ ይላል? በአምላክ ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ እኮ ነው! ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ማን ኀጢአትን ሊያሰተሰርይ ይችላል?” ብለው አሰቡ።
8 ኢየሱስም ወዲያው በልባቸው የሚያስቡትን በመንፈሱ ተረድቶ፣ “እንዴት እንዲህ ታስባላችሁ?
9 ሽባውን፣ ‘ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል’ ከማለትና፣ ‘ተነሥተህ ዐልጋህን ተሸክመህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል?
10 ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢአትን ለማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ” በማለት ሽባውን፣