19 እንዲሁም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
20 ከዚያም ኢየሱስ ወደ አንድ ቤት ገባ፤ እርሱና ደቀ መዛሙርቱ ምግብ መብላት እንኳ እስኪሳናቸው ድረስ ሕዝቡ እንደ ገና በብዛት ተሰበሰበ።
21 ሁኔታውን የሰሙ ዘመዶቹም፣ “አእምሮውን ስቶአል” በማለት ይዘውት ለመሄድ ወዳለበት መጡ።
22 ከኢየሩሳሌም የመጡ ጸሐፍትም፣ “ብዔልዜቡል አድሮበታል፤ አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” አሉ።
23 እርሱም ጠራቸውና በምሳሌ እንዲህ አላቸው፤ “ሰይጣን ሰይጣንን እንዴት ሊያስወጣ ይችላል?
24 እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሊጸና አይችልም፤
25 ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ሊቆም አይችልም።