30 ይህንንም ያለው፣ “ርኩስ መንፈስ አለበት” ስላሉት ነበር።
31 ከዚህ በኋላ እናቱና ወንድሞቹ መጡ፤ በውጭ ቆመውም ሰው ልከውበት አስጠሩት።
32 በዙሪያው የተቀመጡ ብዙ ሰዎችም፣ “እነሆ፤ እናትህና ወንድሞችህ ውጭ ይፈልጉሃል” አሉት።
33 እርሱም መልሶ፣ “እናቴ ማን ናት ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አላቸው።
34 በዙሪያው ወደ ተቀመጡትም በመመልከት፣ እንዲህ አለ፤ “እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው!
35 የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ፣ እኅቴ፣ እናቴም ነውና።”