1 በሌላ ጊዜ ደግሞ በባሕሩ አጠገብ ያስተምር ጀመር። እርሱ ባለበት አካባቢ እጅግ ብዙ ሕዝብ ስለ ተሰበሰበ፣ በባሕሩ ላይ ወዳለች ጀልባ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ባለው ስፍራ ላይ ተሰብስቦ ነበር።
2 እርሱም ብዙ ነገሮችን በምሳሌ አስተማራቸው፤ እንዲህም አላቸው፤
3 “ስሙ፤ አንድ ዘሪ ዘር ሊዘራ ወጣ።
4 ዘሩን በሚዘራበትም ጊዜ አንዳንዱ መንገድ ላይ ወደቀ፤ ወፎችም መጥተው ለቅመው በሉት።
5 ሌላው በቂ ዐፈር በሌለበት በጭንጫ ቦታ ላይ ወደቀ፤ ዐፈሩ ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤
6 ፀሓይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፤ ሥር ስላልነበረውም ደረቀ።