21 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “ጌታ ሆይ፤ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” አለው።
22 ኢየሱስም “እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም” አለው።
23 “ስለዚህ መንግሥተ ሰማይ፣ በአገልጋዮቹ እጅ የነበረውን ሂሳብ ለመተሳሰብ የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች።
24 ሂሳቡን ማጣራት እንደ ጀመረም ዐሥር ሺህ ታላንት ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ አቀረቡለት።
25 አገልጋዩም ያለበትን ዕዳ መክፈል ስላቃተው እርሱ ራሱ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹና ንብረቱ ሁሉ ተሽጠው ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።
26 “በዚህ ጊዜ አገልጋዩ እግሩ ላይ ወድቆ፣ ‘ታገሰኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ ሲል ለመነው።
27 ጌታውም አዘነለትና ማረው፤ ዕዳውንም ትቶለት አሰናበተው።