1 በዚያን ወራት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።
2 ስብከቱም፣ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” የሚል ነበር።
3 በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረለት እርሱ ነው፤“በምድረ በዳ፣‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ጎዳናውንም አስተካክሉ’ እያለ የሚጮህ ድምፅ።”
4 የዮሐንስ ልብስ የግመል ጠጕር ሲሆን፣ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበር። ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበር።
5 ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ዙሪያ ካለው አገር ሁሉ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይጐርፉ፣
6 ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር።
7 ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንት የእፉኝት ልጆች! ለመሆኑ ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ