25 እንግዲህ አጋር በዐረብ አገር ያለችው የሲናን ተራራ በመወከል፣ አሁን ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፤ ከልጇ ጋር በባርነት ናትና።
26 ከላይ የሆነችው ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት ትኖራለች፤ እርሷም እናታችን ናት።
27 እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፤“አንቺ የማትወልጅ መካን ሆይ፤ደስ ይበልሽ፤አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣በእልልታ ጩኺ፤ባል ካላት ይልቅ፣የብቸኛዪቱ ልጆች በዝተዋልና።”
28 እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ እናንተም እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ።
29 በዚያን ጊዜ እንደ ሥጋ ልማድ የተወለደው፣ ልጅ በመንፈስ ኀይል የተወለደውን አሳደደው፤ አሁንም እንደዚያው ነው።
30 ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? “ባሪያዪቱን ከልጇ ጋር አስወግዳት፤ የባሪያዪቱ ልጅ ከነጻዪቱ ልጅ ጋር አይወርስምና” ይላል።
31 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ የነጻዪቱ እንጂ የባሪያዪቱ ልጆች አይደለንም።