1 ሳሙኤል 9:22-27 NASV

22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አመጣ፤ ከተጋበዙትም ሠላሳ ያህል ሰዎች ሁሉ በላይ አስቀመጣቸው።

23 ሳሙኤልም ወጥ ቤቱን፣ “ለይተህ አስቀምጥ ብዬ የሰጠሁህን የሥጋ ብልት አምጣው” አለው።

24 ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፣ “ይህ፣ ‘እንግዶችን ጋብዣለሁ’ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለ ሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋር አብሮ በላ።

25 ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋር ተነጋገረ።

26 በማለዳ ተነሡ፤ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፣ “ላሰናብትህ ስለ ሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፣ ከሳሙኤል ጋር ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

27 ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፣ ሳሙኤል ሳኦልን፣ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም እንደ ተነገረው አደረገ፤ ከዚህ በኋላ ሳሙኤል፣ “አንተ ግን ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክት እነግርህ ዘንድ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቈይ” አለው።