1 በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና አናጢዎችን ከዝግባ ዕንጨት ጋር ላከ።
2 ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ አንግሦ እንዳጸናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት አስተዋለ።
3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም ብዙ ሚስቶች አገባ፤ ከእነርሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
4 በዚያ ሳለ የወለዳቸው የልጆቹ ስም ይህ ነው፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፣
5 ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
6 ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣
7 ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት።