1 ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለ።
2 ከዚያም ዳዊት፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣ የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከም” ሲል አዘዘ።
3 ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ እስራኤልን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
4 የአሮንን ዘሮችና ሌዋውያኑንም በአንድነት ሰበሰበ፤
5 ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
6 ከሜራሪ ዘሮች፣አለቃውን ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤