4 የአሮንን ዘሮችና ሌዋውያኑንም በአንድነት ሰበሰበ፤
5 ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
6 ከሜራሪ ዘሮች፣አለቃውን ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
7 ከጌድሶን ዘሮች፣አለቃውን ኢዮኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤
8 ከኤሊጻፋን ዘሮች፣አለቃውን ሸማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤
9 ከኬብሮን ዘሮች፣አለቃውን ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
10 ከዑዝኤል ዘሮች፣አለቃውን አሚናዳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።