23 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።
24 ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።
25 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ምስጋናውም ብዙ ነው፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።
26 የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
27 በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤ብርታትና ደስታም በማደሪያው ስፍራ።
28 የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርና ኀይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።
29 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ስገዱ።