6 እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘወትር በእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ፊት መለከት እንዲነፉ ተመደቡ።
7 በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤
8 ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ ስሙንም ጥሩ፤ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤
9 ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤
10 በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።
11 ወደ እግዚአብሔርና ወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤ዘወትር ፊቱን ፈልጉ።
12 ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤