6 የዛራ ወንዶች ልጆች፤ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፤ ባጠቃላይ አምስት ናቸው።
7 የከርሚ ወንድ ልጅ አካን፤እርሱም ፈጽሞ መደምሰስ የነበረበትን ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።
8 የኤታን ወንድ ልጅ፤አዛርያ።
9 የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።
10 አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
11 ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።
12 ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ።