16 የጌርሳም ዘሮች፤ሱባኤል።
17 የአልዓዛር ዘሮች፤የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።
18 የይስዓር ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ሰሎሚት።
19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።
20 የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።
21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ ሙሲ።የሞሐሊ ወንዶች ልጆች፤አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።
22 አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው።