14 በዐሥራ አንደኛው ወር ዐሥራ አንደኛው የበላይ አዛዥ ከኤፍሬም ወገን የሆነው ጲርዓቶናዊው በናያስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
15 በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛው የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተ ሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ።
16 የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤በስምዖን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ።
17 በሌዊ ነገድ ላይ የተሾመው የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ፤በአሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።
18 በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።
19 በዛብሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ፤በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት።
20 በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዛዝያ ልጅ ሆሴዕ፤በምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የተሾመው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል።